በGoogle ላይ ስላለዎት ግላዊነት ማወቅ ይፈልጋሉ?
ወደ ትክክለኛው ቦታ ነው የመጡት! ልጆች በብዛት ሊጠይቋቸው የሚችሏቸው ጥያቄዎችን ያንብቡ፣ ለምሳሌ ወላጅዎ እንዴት በGoogle ነገሮችዎ፣ Google ምን መረጃ እንደሚጠቀም እና በተጨማሪ ነገሮች ላይ ሊያግዙዎት እንደሚችሉ።
ወላጆች፣ ይህ መረጃ በFamily Link የሚተዳደሩ የGoogle መለያዎችን፣ ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት (ወይም በአገርዎ ከሚመለከተው ዕድሜ) በታች የሆኑ ልጆችን ብቻ ነው የሚመለከተው። ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት የእኛን የግላዊነት ማስታወቂያ እና የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።
የመለያዬ ኃላፊ ማነው?
የእርስዎ ወላጅ የGoogle መለያዎ ኃላፊ ናቸው። እሱን እንዲያቀናብሩ ለማገዝ Family Link የሚባል መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ። ዕድሜዎ ገፋ ሲል የመለያዎን ኃላፊነት መውሰድ ይችላሉ።
የእርስዎ ወላጆች እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ፦
- ወደ የእርስዎ መለያ መግባት፣ የመለያዎን ይለፍ ቃል መቀየር ወይም መለያዎን መሰረዝ።
- የእርስዎን ስልክ ወይም ጡባዊ መቆለፍ።
- የእርስዎ ስልክ ወይም ጡባዊ የት እንዳለ ማየት።
- እርስዎ ምን መተግበሪያዎችን መጠቀም እንደሚችሉ መምረጥ።
- እርስዎ መተግበሪያዎችዎን ለምን ያህል ጊዜ እንደሚጠቀሙ ማየት።
- እንደ Google ፍለጋ፣ YouTube ወይም Google Play ባሉ አንዳንድ የGoogle መተግበሪያዎች ውስጥ የሚያዩዋቸውን ነገሮች መቀየር።
- የእርስዎን የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች መምረጥ። (እነዚህ ቅንብሮች እርስዎ Google ላይ ምን እንደሚያደርጉ ላይ መረጃን የሚያስቀምጡ ናቸው።)
- ለመተግበሪያዎችዎ ቅንብሮችን እና ፈቃዶችን መምረጥ።
- ለመለያዎ ስም፣ የልደት ቀን እና ሌላ መረጃ መምረጥ።
- እንደ Google Play ባሉ አንዳንድ የGoogle ምርቶች ውስጥ ምን ማውረድ ወይም መግዛት እንደሚችሉ መምረጥ።
እንዴት እና ለምንድነው Google የእኔን መረጃ የሚጠቀምበት?
እንደ የእርስዎ ስም እና የልደት ቀን ያለ እርስዎ ወይም ወላጅዎ የምትሰጡንን መረጃ ልናስቀመጥ እንችላለን። እንዲሁም እርስዎ የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ሲጠቀሙ መረጃን ልናስቀምጥ እንችላለን። የዚህን መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ተግተን እንሰራለን፣ እና ለተለያዩ ምክንያቶች እንጠቀምበታለን — እንደ የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ይበልጥ አጋዥ ማድረግ ያሉ።
ከእርስዎ ወላጅ ጋር በመሆን መረጃዎን ልንጠቀምበት ስለምንችልባቸው መንገዶች ተጨማሪ ይወቁ፦
- የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች እንዲሰሩ ማድረግ፦ ለምሳሌ፣ በGoogle ፍለጋ ላይ «ቡችላዎች» ከፈለጉ ስለቡችላዎች ያሉ ነገሮችን ለእርስዎ ለማሳየት መረጃዎን እንጠቀምበታለን።
- የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች የተሻሉ ማድረግ፦ ለምሳሌ፣ የሆነ ነገር ከተበላሸ እሱን ለማስተካከል መረጃ መጠቀም እንችላለን።
- Googleን፣ የእኛ ተጠቃሚዎችን እና ሕዝቡን ለመጠበቅ፦ ሰዎችን መስመር ላይ ደህንነታቸውን በይበልጥ ለመጠበቅ መረጃን እንጠቀማለን።
- አዲስ መተግበሪያዎችን እና ጣቢያዎችን መስራት፦ መገንባት ለምንችላቸው አዲስ የGoogle ነገሮች አዲስ ሐሳቦችን ለማግኘት ሰዎች የአሁኖቹን የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው እንማራለን።
- ሊወዷቸው የሚችሏቸው ነገሮችን ለእርስዎ ማሳየት፦ ለምሳሌ፣ እርስዎ በYouTube Kids ላይ የእንስሳት ቪዲዮዎችን ማየት የሚወድዱ ከሆነ ተጨማሪ ልናሳየዎት እንችላለን።
- እንደ እርስዎ ባሉበት ጣቢያዎች ባሉ ነገሮች ላይ ተመስርተን ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ማሳየት።
- እርስዎን መረጃ ለማሳወቅ፦ ለምሳሌ፣ መልዕከት ለእርስዎ ለመላክ የኢሜይል አድራሻዎን ልንጠቀምበት እንችላለን። እርስዎ ከማያውቁት ሰው የመጡ መልዕክቶችን ከመክፈትዎ በፊት ሁልጊዜ ወላጅ ይጠይቁ።
Google ምን ማስቀመጥ እንደሚችል መንገር እችላለሁ?
አዎ፣ ስለእርስዎ የምናስቀምጣቸው አንዳንድ ነገሮችን መቀየር ይችላሉ። እንደ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ባሉ አንዳንድ የግላዊነት ቅንብሮች ላይ ለውጦችን ካደረጉ ወላጅዎን እናሳውቃለን። እነሱም እርስዎ ቅንብሮችዎን እንዲቀይሩ ማገዝ ይችላሉ።
እርስዎ እና ወላጅዎ በማንኛውም ጊዜ ስለእርስዎ እና ስለGoogle መለያዎ ያለ አንዳንድ መረጃን መመልከት እና ማቀናበር ትችላላችሁ።
Google የግል መረጃዬን ለሌሎች ያጋራል?
እንደ የእርስዎ ስም ያለ የግል መረጃዎን ከGoogle ውጭ የምናጋራባቸው ጥቂት ምክንያቶች አሉ። ይህን መረጃ ካጋራነው መጠበቁን ለማረጋገጥ እርምጃዎች እንወስዳለን።
የተወሰነ የግል መረጃ ልናጋራ እንችላለን፦
- Google ላይ ላሉ የእርስዎ ወላጅ እና የቤተሰብ ቡድን
- አብረን ለምንሰራቸው ኩባንያዎች
- የእርስዎ ወላጅ ችግር የለውም ሲሉን
- ለሕጋዊ ምክንያቶች ሲያስፈልግን
መስመር ላይ የማጋራውን ነገር ሌላ ማን ማየት ይችላል?
እንደ ኢሜይሎች ወይም ፎቶዎች ያለ መስመር ላይ የሚያጋሩት ማንኛውም ነገር በብዙ ሰዎች ሊታይ ይችላል። ለሚያምኗቸው ሰዎች ብቻ ያጋሩ። እርግጠኛ ካልሆኑ ወላጅ ወይም የቤተሰብ አባል ይጠይቁ።
ተጨማሪ ማወቅ ይፈልጋሉ? የእርስዎ ወላጅ የእኛን የግላዊነት መመሪያ እንዲያነብቡ እንዲያግዙዎት ይጠይቋቸው።
በGoogle ላይ ስላለዎት ግላዊነት ማወቅ ይፈልጋሉ?
ወደ ትክክለኛው ቦታ ነው የመጡት! እዚህ እርስዎ የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ሲጠቀሙ Google እንዴት መረጃዎን እንደሚሰበስብና እንደሚጠቀም ተጨማሪ ማወቅ የሚችሉበት ቦታ ነው። እንዲሁም ወላጅዎ እርስዎ እንዴት የGoogle መለያዎን እና መሣሪያዎችዎን ማቀናበር እንደሚችሉ ላይ ሊያግዙዎት ይችላሉ።
ወላጆች፣ ይህ መረጃ በFamily Link የሚተዳደሩ የGoogle መለያዎችን፣ ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት (ወይም በአገርዎ ከሚመለከተው ዕድሜ) በታች የሆኑ ልጆችን ብቻ ነው የሚመለከተው። ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት የእኛን የግላዊነት ማስታወቂያ እና የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።
የመለያዬ ኃላፊ ማነው?
አሁን የእርስዎ ወላጅ የGoogle መለያዎ ኃላፊ ነው። መለያዎን ራስዎ ማስተዳደር የሚችሉበት ዕድሜ እስከሚደርሱ ድረስ እነርሱ መለያዎን እንዲያቀናብሩ ለማገዝ Family Link የሚባል መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ።
የእርስዎ ወላጆች እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ፦
- ወደ የእርስዎ መለያ መግባት፣ የመለያዎን ይለፍ ቃል መቀየር ወይም መለያዎን መሰረዝ።
- እንደ ስልኮች ወይም ጡባዊዎች ያሉ መሣሪያዎችዎን መቼ እና ምን ያህል ጊዜ መጠቀም እንደሚችሉ ላይ ገደቦችን ማቀናበር።
- የእርስዎ ስልክ ወይም ጡባዊ የት እንዳለ ማየት።
- እርስዎ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን መተግበሪያዎች መምረጥ።
- እርስዎ መተግበሪያዎችዎን ለምን ያህል ጊዜ እንደሚጠቀሙ ማየት።
- እንደ Google ፍለጋ፣ YouTube ወይም Google Play ላሉ አንዳንድ የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች የይዘት ቅንብሮችን ማቀናበር። እነዚህ ቅንብሮች እርስዎ ምን እንደሚያዩ መቀየር ይችላሉ።
- እርስዎ ራስዎ እነዚህን መቆጣጠሪያዎች እንዳያቀናበሩ ማገድ ጨምሮ እንደ የYouTube ታሪክ ያለ የመለያዎን የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ማቀናበር።
- እንደ መተግበሪያዎች የእርስዎን ማይክሮፎን፣ ካሜራ ወይም እውቂያዎች መጠቀም ይችሉ እንደሆነ ያሉ በእርስዎ ስልክ ወይም ጡባዊ ላይ የመተግበሪያዎች ፈቃዶችን መገምገም።
- እንደ የእርስዎ ስም፣ ጾታ ወይም ትውልድ ቀን ያለ የመለያዎ መረጃን መመልከት፣ መቀየር ወይም መሰረዝ።
- እንደ Google Play ባሉ አንዳንድ የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ውስጥ የእርስዎን ውርዶች እና ግዢዎች ማፅደቅ።
እንዴት እና ለምንድነው Google የእኔን መረጃ የሚጠቀምበት?
ልክ እንደ አብዛኛዎቹ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ሁሉ እንደ የእርስዎ ስም እና የልደት ቀን ያለ እርስዎ ወይም አንድ ወላጅ የሚሰጡንን መረጃ እንሰበስባለን፣ እና እርስዎ የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ሲጠቀሙ መረጃ እንሰበስባለን። የዚህ መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ተግተን እንሰራለን፣ እና እንደ የእኛን ምርቶች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ ማድረግ ላሉ ነገሮች እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ የሚከተሉትን ለማድረግ ውሂብ እንሰበስባለን፦
- የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች እንዲሰሩ ማድረግ፦ ለምሳሌ፣ በGoogle ፍለጋ ላይ «ስፖርት» ከፈለጉ ስለስፖርት ያሉ ነገሮችን ለእርስዎ ለማሳየት መረጃዎን እንጠቀምበታለን።
- የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች የተሻሉ ማድረግ፦ ለምሳሌ፣ የሆነ ነገር ከተበላሸ እሱን ለማስተካከል መረጃ መጠቀም እንችላለን።
- Googleን፣ የእኛ ተጠቃሚዎችን እና ሕዝቡን ለመጠበቅ፦ እንደ ማጭበርበርን ማግኘት እና መከላከል ያለ ሰዎች መስመር ላይ ደህንነታቸውን በይበልጥ ለመጠበቅ መረጃን እንጠቀማለን።
- አዲስ መተግበሪያዎችን እና ጣቢያዎችን መስራት፦ መገንባት ለምንችላቸው አዲስ የGoogle ምርቶች አዲስ ሐሳቦችን ለማግኘት ሰዎች የአሁኖቹን የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው እንማራለን።
- መረጃን ለእርስዎ ግላዊነት ማላበስ፣ ይህ ማለት እኛ ሊወዷቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮችን ለእርስዎ ማሳየት። ለምሳሌ፣ በYouTube Kids ላይ የእንስሳት ቪዲዮዎችን መመልከት የሚወድዱ ከሆነ ተጨማሪ የሚመለከቷቸውን ልንመክር እንችላለን።
- እንደ እርስዎ ባሉበት ጣቢያዎች ባሉ ነገሮች ላይ ተመስርተን ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ማሳየት።
- እርስዎን መረጃ ለማሳወቅ፦ ለምሳሌ፣ እንደ የደህንነት ስጋት ካለ መልዕከት ለእርስዎ ለመላክ የኢሜይል አድራሻዎን ልንጠቀምበት እንችላለን። እርስዎ ከማያውቁት ሰው የመጡ መልዕክቶችን ከመክፈትዎ በፊት ሁልጊዜ ወላጅ ይጠይቁ።
Google ምን ማስቀመጥ እንደሚችል መንገር እችላለሁ?
አዎ፣ ስለእርስዎ የምናስቀምጣቸው አንዳንድ ነገሮችን መቀየር ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የእርስዎ YouTube ታሪክ በGoogle መለያዎ ላይ እንድናስቀምጥ ካልፈለጉ የYouTube ታሪክን ማጥፋት ይችላሉ። እንደ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ባሉ አንዳንድ የግላዊነት ቅንብሮች ላይ ለውጦችን ካደረጉ ወላጅዎን እናሳውቃለን። እነሱም እርስዎ ቅንብሮችዎን እንዲቀይሩ ማገዝ ይችላሉ።
እርስዎ እና ወላጅዎ በማንኛውም ጊዜ ስለእርስዎ እና ስለGoogle መለያዎ ያለ አንዳንድ መረጃን መመልከት እና ማቀናበር ትችላላችሁ።
Google የግል መረጃዬን ለሌሎች ያጋራል?
እንደ የእርስዎ ስም እና የኢሜይል አድራሻ ያለ የግል መረጃዎን ከGoogle ውጭ የምናጋራባቸው ጥቂት ምክንያቶች አሉ። ይህን መረጃ ካጋራነው መጠበቁን ለማረጋገጥ እርምጃዎች እንወስዳለን።
የተወሰነ የግል መረጃ ልናጋራ እንችላለን፦
- Google ላይ ላሉ የእርስዎ ወላጅ እና የቤተሰብ ቡድን
- አብረን ለምንሰራቸው ኩባንያዎች
- የእርስዎ ወላጅ ችግር የለውም ሲሉን
- ለሕጋዊ ምክንያቶች ሲያስፈልግን
መስመር ላይ የማጋራውን ነገር ሌላ ማን ማየት ይችላል?
እንደ ኢሜይሎች ወይም ፎቶዎች ያለ መስመር ላይ የሚያጋሩት ማንኛውም ነገር በብዙ ሰዎች ሊታይ ይችላል። አንዴ መስመር ላይ ከተጋራ በኋላ እሱን ማስወገድ ከባድ ሊሆን ይችላል። ለሚያምኗቸው ሰዎች ብቻ ያጋሩ። እርግጠኛ ካልሆኑ ወላጅ ወይም የቤተሰብ አባል ይጠይቁ።
ተጨማሪ ማወቅ ይፈልጋሉ? የእርስዎ ወላጅ የእኛን የግላዊነት መመሪያ እንዲያነብቡ እንዲያግዙዎት ይጠይቋቸው።
በGoogle ላይ ስላለዎት ግላዊነት ማወቅ ይፈልጋሉ?
እዚህ እርስዎ የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ሲጠቀሙ Google እንዴት መረጃዎን እንደሚሰበስብና እንደሚጠቀም ተጨማሪ ማወቅ የሚችሉበት ቦታ ነው። እንዲሁም ወላጅዎ እርስዎ እንዴት የGoogle መለያዎን እና መሣሪያዎችዎን ማቀናበር እንደሚችሉ ላይ ሊያግዙዎት ይችላሉ።
ይህ መረጃ በFamily Link የሚተዳደሩ የGoogle መለያዎችን፣ የራሳቸውን መለያ ለማቀናበር ከሚፈለገው የዕድሜ መስፈርት በታች የሆኑ ልጆችን እና ታዳጊዎችን ብቻ ነው የሚመለከተው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የእኛን የግላዊነት ማስታወቂያ እና የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።
ወላጄ የእኔን መለያ ማቀናበር ላይ ማገዝ ይችላሉ?
የእርስዎ ወላጅ የተወሰኑ የGoogle መለያዎ ገጽታዎችን ለማቀናበር Family Link የሚባል መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ። በእርስዎ መሣሪያ ላይ የሚወሰን ሆኖ እንደሚከተሉት ያሉ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ፦
- ወደ የእርስዎ መለያ መግባት፣ የመለያዎን ይለፍ ቃል መቀየር ወይም መለያዎን መሰረዝ።
- መሣሪያዎችዎን ምን ያህል ጊዜ እና መቼ መጠቀም እንደሚችሉ ላይ ገደቦችን ማቀናበር።
- በመለያ የገቡ እና ንቁ የእርስዎ መሣሪያዎች አካባቢን መመልከት።
- መተግበሪያዎችዎን ማቀናበር እና እርስዎ ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠቀሙባቸው ማየት።
- እንደ Google ፍለጋ፣ YouTube ወይም Google Play ላሉ አንዳንድ የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች የይዘት ቅንብሮችን ማቀናበር። እነዚህ ቅንብሮች እርስዎ ምን እንደሚያዩ መቀየር ይችላሉ።
- እርስዎ ራስዎ እነዚህን መቆጣጠሪያዎች እንዳያቀናበሩ ማገድ ጨምሮ እንደ የYouTube ታሪክ ያለ የመለያዎን የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎች ማቀናበር።
- እንደ መተግበሪያዎች የእርስዎን ማይክሮፎን፣ ካሜራ ወይም እውቂያዎች መጠቀም ይችሉ እንደሆነ ያሉ በእርስዎ መሣሪያ ላይ የመተግበሪያዎች ፈቃዶችን መገምገም።
- እንደ የእርስዎ ስም፣ ጾታ ወይም ትውልድ ቀን ያለ የመለያዎ መረጃን መመልከት፣ መቀየር ወይም መሰረዝ።
- እንደ Google Play ባሉ አንዳንድ የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ውስጥ የእርስዎን ውርዶች እና ግዢዎች ማፅደቅ።
እንዴት እና ለምንድነው Google የእኔን መረጃ የሚሰበስበው እና የሚጠቀምበት?
ልክ እንደ አብዛኛዎቹ ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ሁሉ እንደ የእርስዎ ስም እና የልደት ቀን ያለ እርስዎ ወይም አንድ ወላጅ የሚሰጡንን መረጃ እንሰበስባለን፣ እና እርስዎ የእኛን መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ሲጠቀሙ መረጃ እንሰበስባለን። የዚህ መረጃ ደህንነት ለመጠበቅ ተግተን እንሰራለን፣ እና እንደ የእኛን ምርቶች ለእርስዎ ይበልጥ ጠቃሚ ማድረግ ላሉ ነገሮች እንጠቀምበታለን። ለምሳሌ፣ የሚከተሉትን ለማድረግ ውሂብ እንሰበስባለን፦
- Googleን፣ የእኛ ተጠቃሚዎችን እና ሕዝቡን ለመጠበቅ፦ እንደ ማጭበርበርን ማግኘት እና መከላከል ያለ ሰዎች መስመር ላይ ደህንነታቸውን በይበልጥ ለመጠበቅ ውሂብን እንጠቀማለን።
- አገልግሎቶቻችንን ማቅረብ፦ እንደ ውጤቶችን መመለስ እንድንችል እርስዎ የፈለጓቸውን ቃላት ማሰናዳት ያሉ አገልግሎቶቻችንን ለማቅረብ ውሂብን እንጠቀማለን።
- የእኛን አገልግሎቶች መጠገን እና ማሻሻል፦ ለምሳሌ፣ የእኛ ምርቶች መስራት ባለባቸው መንገድ መስራት ሲያቆሙ መከታተል እንችላለን። እና የትኛዎቹ የፍለጋ ቃላት ፊደል በተደጋጋሚነት በስህተት እንደሚጻፉ መረዳት በመላ አገልግሎቶቻችን ላይ የምንጠቀምባቸው የፊደል ማረሚያ ባህሪያትን እንድናሻሽል ያግዘናል።
- አዲስ ምርቶችን መገንባት፦ ውሂብ አዲስ አገልግሎቶችን እንድንገነባ ያግዘናል። ለምሳሌ፣ ሰዎች የመጀመሪያው የGoogle ፎቶዎች መተግበሪያ በሆነው Picasa ውስጥ ፎቶዎቻቸውን እንዴት እንዳደራጁ መረዳት Google ፎቶዎችን ለመንደፍ እና ለማስጀመር አግዞናል።
- ይዘትን ግላዊነት ማላበስ፣ ይህ ማለት እኛ ሊወዷቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸው ነገሮችን ለእርስዎ ማሳየት። ለምሳሌ፣ በYouTube ላይ የስፖርት ቪዲዮዎችን መመልከት የሚወድዱ ከሆነ ተጨማሪ የሚመለከቷቸውን ልንመክር እንችላለን።
- እንደ እርስዎ ያሉበት ጣቢያ፣ ያስገቧቸው የፍለጋ ቃላት ወይም የእርስዎ ከተማና ክልል ባለ መረጃ ላይ ተመስርተን ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ማሳየት።
- አፈጻጸምን መለካት፦ አፈጻጸምን ለመለካት እና የእኛ አገልግሎቶች እንዴት ስራ ላይ እንደሚውሉ ለመረዳት ውሂብን እንጠቀማለን።
- እርስዎን መረጃ ለማሳወቅ፦ ለምሳሌ፣ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ካገኘን ማሳወቂያ ለእርስዎ ለመላክ የኢሜይል አድራሻዎን ልንጠቀምበት እንችላለን።
እንዴት ነው Google ምን ማስቀመጥ እንደሚችል መወሰን የምችለው?
በእርስዎ ቅንብሮች አማካኝነት እኛ የምንሰበስበውን ውሂብ እና ይህ ውሂብ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል መገደብ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የእርስዎ YouTube ታሪክ በGoogle መለያዎ ላይ እንድናስቀምጥ ካልፈለጉ የYouTube ታሪክን ማጥፋት ይችላሉ። እርስዎ በእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያዎችዎ ላይ ለውጦችን ካደረጉ የእርስዎ ወላጅ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። ስለግላዊነት ቅንብሮችዎ ተጨማሪ ይወቁ
እርስዎ በማንኛውም ጊዜ ስለእርስዎ እና ስለGoogle መለያዎ ያለ አንዳንድ መረጃን መመልከት እና ማቀናበር ትችላላችሁ።
Google የግል መረጃዬን ለሌሎች ያጋራል?
የእርስዎን የግል መረጃ እንደ በህግ ከተፈለገ ካሉ የተወሰኑ ሁኔታዎች በስተቀር ከGoogle ውጭ ላሉ ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች አናጋራም። ይህን መረጃ ካጋራነው መጠበቁን ለማረጋገጥ እርምጃዎች እንወስዳለን።
የተወሰነ የግል መረጃ ልናጋራ እንችላለን፦
- Google ላይ ላሉ የእርስዎ ወላጅ እና የቤተሰብ ቡድን
- እርስዎ እና ወላጅዎ ፈቃድ ስትሰጡን፣ ወይም ለህጋዊ ምክንያቶች። ለሚከተሉት አስፈላጊ ነው ብለን ካመነን የግል መረጃን ከGoogle ውጭ ልናጋራ እንችላለን፦
- ማንኛውም የሚመለከተው ህግ፣ ደንብ፣ የህግ አካሄድ ወይም የመንግስት ጥያቄን ለማስፈጸም የሚያስፈልገውን መስፈርት አሟልቶ መገኘት።
- ጥሰቶች ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን መመርመር ጨምሮ የሚመለከተውን የአገልግሎት ውል መፈጸም።
- የማጭበርበር፣ የደህንነት ወይም ቴክኒካዊ ችግሮችን ማግኘት፣ መከላከል ወይም አጸፋ መስጠት።
- ህግ በሚያዝዘው ወይም በሚፈቅደው መልኩ የGoogle፣ የእኛ ተጠቃሚዎች ወይም የሕዝቡ መብቶችን፣ ንብረቶችን ወይም ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ጉዳትን መከላከል።
- ለውጫዊ ማሰናዳት። አብረን የምንሰራቸው ኩባንያዎች እኛ በምንሰጣቸው ትዕዛዞች መሠረት ውሂብ እንዲያሰናዱ የግል መረጃ እናቀርብላቸዋለን። ለምሳሌ፣ በደንበኛ ድጋፍ ላይ እንዲያግዙን ውጫዊ ኩባንያዎችን እንጠቀማለን፣ እና ለተጠቃሚ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እንዲቻል የግል መረጃ ማጋራት አለብን።
ሌላ ማነው እንደ ፎቶዎች፣ ኢሜይል እና ሰነዶች ያሉ እኔ የማጋራቸው ነገሮችን ማየት የሚችለው?
እርስዎ በሚጠቀሙባቸው የGoogle መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ውስጥ የተወሰነ መረጃ ለሌሎች ሰዎች ለማጋራት መምረጥ ይችላሉ።
እርስዎ ሲያጋሩ ሌሎች ሰዎች ከGoogle ውጭ ባሉ መተግበሪያዎች እና ጣቢያዎች ውስጥም እንኳ ዳግም ሊያጋሩት እንደሚችሉ አይርሱ።
በማንኛውም ጊዜ የራስዎን ይዘት ከመለያዎ መሰረዝ ይችላሉ፣ ነገር ግን ይህ እርስዎ አስቀድመው ያጋሯቸውን ቅጂዎችን አይሰርዝም።
ምን እንደሚያጋሩ ላይ በደንብ ያስቡበት፣ እና ለሚያምኗቸው ሰዎች ብቻ ያጋሩ።
ስለእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ተጨማሪ ለማወቅ በማንኛውም ጊዜ የእኛን የግላዊነት መመሪያ መመልከት ይችላሉ።